ከዘጠኝ ሺህ በላይ ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ2.8 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት ተፈራረሙ።
”PAPDA” የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በኮንሶ ዞን ሴቶችና ህፃናትን ጉዳይ መምሪያና ሌሎች በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል።
_____________________
ድርጅቱ በካራት እና ሠገን ዙሪያ ወረዳ በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች፣ ሴቶች እና ህፃናት ላይ በጤና፣ ፆታዊ ትንኮሳ መከላከል፣ ንፅህና አጠባበቅ፣ አቅም ግንባታ እና በሌሎች ተግባራት ዙሪያ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።
የ3 ወር ቆይታ ይኖረዋል የተባለው ”PAPDA” ፕሮጀክት በሁለቱ ወረዳዎች ላይ ተጠቃሚ ከሚሆኑ 9,600 የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ 6,000 በላይ ሴቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታውቋል።
ፕሮጀክቱ በኮንሶ ዞን አላማ ለማስፈፀም ከ2.8 ሚሊየን ብር በላይ የፕሮጀክት ሰነድ ተፈራርመዋል።
የኮንሶ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዝናሽ ቢታማ እንደገለፁት፤ እንደ ዞን የተከሰተውን ችግር ለመጋራት የመጣውን ድርጅት ከልብ አመስግነው በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የዞኑ ግብር መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፈነ ትጫሮ በበኩላቸው በተለያዩ ጊዜያት በግጭት ምክንያት የተጎዱ ወገኖች፣ ማህበራዊ መገልገያ ተቋማት፣ የውሃ ማሰራጫ ቧቧዎች እና ሌሎች የግልና የመንግስት ቤትና ንብረት በመውደሙ የህዝቡ ጉዳት ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደይጋንቶ ኡርማሌ በበኩላቸው ድርጅቱ በሴቶችና ህፃናት ጤና ላይ ትኩረት በማድረጉ PAPDA’ን (ፓርትነር ሺፕ ፎር ፓስቶራሊስት ዴቨሎፕመንት አሶስየሽን) ድርጅትን አድንቀዋል።
የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባ በበኩላቸው ድርጅቱ ህብረተሰቡን ለመደገፍ ያመጣውን ድጋፍ አድንቀው፤ በኮንሶ ከተከሰተው ችግርና ስፋት አንፃር የፕሮጀክቱ የ3 ወር ቆይታ በቂ ባለመሆኑ በሌላ ፕሮግራም ቀጣይነት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል።
ይህ ሥራ ማስጀመሪያ ነው ያሉት የ”PAPDA” ፕሮጀክት ኦፕሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ የሱፍ፤ በቀጣይ ሰፋ ባለ ፕሮጀክትና ድጋፎች የኮንሶን ማህበረሰብ እንደሚደግፉ አስታውቀው፤ ቆይታቸውን በሌላ ፕሮጀክት እንደሚያራዝሙ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ድርጅቱ ከኮንሶ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ፣ ግብርና መምሪያ እና ጤና መምሪያ ጋር በሥራ ሰነዶች ላይ የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
 
Partnership for Pastoralist Development Association (PAPDA) will implement  a project proposal entitled GBV prevention, Risk mitigation and response for communities affected by conflict in Konso zone,karat and Segen zuriya woredas
 
The project is located and be implemented; in SNNP Rgional state district of KONSO Zone, karat and Segen zuriya Woreda. The project will directly benefit a total of 9,600 individuals (6,905 female) and 18,393 individuals (14,715 female) indirectly.

 

The overall goal of the project is to increasingly protect women and girls from violence, HTPs, exploitation, discrimination and to rehabilitate them to enjoy and exercise their rights by intervening with activities that link with the women empowerment.

 .

  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *